0 comments
    No comments found
Description

amharic gospel mezmur

Lyrics

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
ኦ ፡ መዳኔ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
የፍቅርህ ፡ ብዛቱ ፡ እንዲህ ፡ ያዘምረኛል
ውለታህ ፡ መች ፡ ዝም ፡ ያሰኛል (፫x)
ላውራ ፡ ማዳንህን ፡ ጌታ
ላውራ ፡ ስራህን ፡ ኢየሱስ (፪x)

ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ ሳነባ
መድረሻ ፡ ጠፍቶኝ ፡ ሆኜ ፡ እምባ ፡ በእምባ
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ የደረሰልኝ
እምባዬን ፡ ጠርጐ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ያለኝ

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ

ጐልያድ ፡ በፊቴ ፡ እንዲያው ፡ ተደንቅሮ
ባስጨነቀኝ ፡ ቁጥር ፡ ሳሰማ ፡ እሮሮ
ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ከተፍ ፡ ያለልኝ
ያንን ፡ ተራራውን ፡ ከፊቴ ፡ ጣለልኝ

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ

በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ጠራሁህ
መታመኛዬ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነህ ፡ አልኩህ
አንተም ፡ አልናከኝም ፡ ቃሌን ፡ ሁሉ ፡ ሰማህ
ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ አባቴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
እንዳንተ ፡ ያለ (፫x) ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔስ ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ አለ
ኦ ፡ መዳኔ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
የፍቅርህ ፡ ብዛቱ ፡ እንዲህ ፡ ያዘምረኛል
ውለታህ ፡ መች ፡ ዝም ፡ ያሰኛል (፫x)
ላውራ ፡ ማዳንህን ፡ ጌታ
ላውራ ፡ ስራህን ፡ ኢየሱስ (፪x)

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads

::
/ ::

Queue