እወድሃለሁ (Ewedihalehu) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

እወድሃለሁ ፡ አጅግ ፡ አብዝቼ
ከልቤ ፡ ጋራ ፡ እጄን ፡ አንስቼ
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ ምገልጸው
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ ፍቅርህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ቃላት ፡ ባገኘሁና
ባወራው ፡ የአንተን ፡ ምስጋና
የልቤ ፡ በደረሰልኝ
አምላኬ ፡ አንተው ፡ ከብረህልኝ

የሚያስፈልገኝ ፡ አንድ ፡ ነገር
እርሱም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር
አንተን ፡ ካገኘሁ ፡ ጠግቤ ፡ አድራለሁ
ስለዚህ ፡ አምላኬ ፡ እወድሃለሁ (፪x)

አዝ፦ ቃላት ፡ ባገኘሁና
ባወራው ፡ የአንተን ፡ ምስጋና
የልቤ ፡ በደረሰልኝ
አምላኬ ፡ አንተው ፡ ከብረህልኝ

መላ ፡ እኔነቴ ፡ አንተን ፡ ይወዳል
በቀን ፡ በለሊት ፡ ልቤ ፡ ያስብሃል
ያላንተ ፡ መኖር ፡ አይሆንልኝም
ሕይወቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሌላም ፡ የለኝም (፪x)

አዝ፦ ቃላት ፡ ባገኘሁና
ባወራው ፡ የአንተን ፡ ምስጋና
የልቤ ፡ በደረሰልኝ
አምላኬ ፡ አንተው ፡ ከብረህልኝ

የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ መድህኔ
ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ (፪x)

ሕይወት ፡ ተገለጠ ፡ እኔም ፡ አይቻለሁ
ጌታ ፡ ቸር ፡ መሆኑን ፡ ቀምሼ ፡ አውቄያለሁ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ በርቶልኛል
ታዲያ ፡ ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ ማንስ ፡ ይለየኛል

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ መድህኔ
ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ መድህኔ
ሰላሜ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ

ሰው ፡ አንተን ፡ ካገኘ ፡ ምን ፡ ያስፈልገዋል
እፎይ ፡ ብሎ ፡ አርፎ ፡ ተደላድሎ ፡ ይኖራል
ፍቅርህ ፡ የሚያጠገብ ፡ ልብን ፡ የሚያረካ
የመኖር ፡ ትርጉሙ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለካ

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ መድህኔ
ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ (፪x)
ዕረፍቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
ሰላሜ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue