Nuroye Bekidan New (ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው)

ሃገር ፡ ምድር ፡ ሲናወጥ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲታገል ፡ ለማምለጥ
እየባሰ ፡ ግር ፡ ግሩ ፡ ሕይወቴን ፡ ሊረብሽ ፡ ሊያስፈሩ
ለካ ፡ ቆሜ ፡ ሳስበው ፡ ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው
ኧረ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ ኪዳን ፡ አለኝ ፡ የእውነትም ፡ ቃል ፡ አለኝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ልጁ ፡ ያደረገኝ
መመኪያዬ ፡ የእውነትም ፡ ተስፋዬ
እርሱ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ መደገፊያዬ (፪x)

እንድጠፋ ፡ ፈልጐ ፡ ያ ፡ ክፉ ፡ ሊወጠኝ ፡ ሲጥር
አልገባውም ፡ መሰለኝ ፡ እንዳለኝ ፡ ሃይለኛ ፡ ቅጥር
ሕይወቴን ፡ ሊተናኮል ፡ ጠጋ ፡ ጠጋ ፡ ሲለኝ
ኪዳኑን ፡ የሚያከብረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ወጣልኝ

እስኪ ፡ በል ፡ ተናገር ፡ አሉኝ
እንዴት ፡ ነው ፡ ሚረዳህ ፡ አሉኝ
ልናገር ፡ አፌን ፡ ሞልቼ
የመጣውን ፡ ከአባቶቼ
ያኔም ፡ አሁንም ፡ ይሰራል
አልፎም ፡ ያድነኛል
የተጻፈውን ፡ ሳምን ፡ የቃልኪዳኑን (፪x)

አዝ፦ ኪዳን ፡ አለኝ ፡ የእውነትም ፡ ቃል ፡ አለኝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ልጁ ፡ ያደረገኝ
መመኪያዬ ፡ የእውነትም ፡ ተስፋዬ
እርሱ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ መደገፊያዬ

በሕይወቴ ፡ ስፈራ ፡ ነገ ፡ ስለሚሆነው ፡ ሳላቅ
ነገ ፡ ስለሚሆነው ፡ አለኝ ፡ ተው ፡ አትጨነቅ
በነጻነት ፡ እንድትኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ነኝ ፡ አለኝ
ይሄ ፡ የእውነት ፡ ኪዳን ፡ እንዳልሰጋ ፡ አረገኝ

አዝ፦ ኪዳን ፡ አለኝ ፡ የእውነትም ፡ ቃል ፡ አለኝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ልጁ ፡ ያደረገኝ
መመኪያዬ ፡ የእውነትም ፡ ተስፋዬ
እርሱ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ መደገፊያዬ

እስኪ ፡ በል ፡ ተናገር ፡ አሉኝ
እንዴት ፡ ነው ፡ ሚረዳህ ፡ አሉኝ
ልናገር ፡ አፌን ፡ ሞልቼ
የመጣውን ፡ ከአባቶቼ
ያኔም ፡ አሁንም ፡ ይሰራል
አልፎም ፡ ያድነኛል
የተጻፈውን ፡ ሳምን ፡ የቃልኪዳኑን (፪x)

አለኝ ፡ ቃልኪዳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ
አለኝ ፡ ቃልኪዳን ፡ እንዴት ፡ ልፈራ (፰x)

Recently Listened by

1 comments

:: / ::
::
/ ::

Queue