Eysus New Mirchaye (ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ)

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ (፪x)

እናት ፡ ልጇን ፡ በጣር ፡ ትወልዳለች
ወልዳ ፡ ጡት ፡ አጥብታ ፡ ታሳድጋለች
በነፍሷ ፡ ላይ ፡ ድንገት ፡ ችግር ፡ ሲመጣ
ወንዝ ፡ ውስጥ ፡ ጣለችው ፡ ሙሴን ፡ አውጥታ
ግን ፡ አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰበሰበው
በንጉሡ ፡ ቤት ፡ በተዓምር ፡ አሳደገው [1]
ለሞት ፡ የተሰጠውን ፡ አነሳና
በህዝቡ ፡ ላይ ፡ ሾመው ፡ ፀጋ ፡ አበዛና [2]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

አጋር ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ ተሰደደች
አባት ፡ በልጁ ፡ ሲጨክን ፡ አየች
ውኃም ፡ አለቀ ፡ ምንዎን ፡ ታጠጣው
ጨነቃትና ፡ እራቀች ፡ ጥላው
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጥኖ ፡ መጣላት
ውሃውን ፡ አየች ፡ ዓይኗን ፡ ከፍቶላት
የሚያያትንም ፡ አየችውና
ቤቷ ፡ መለሳት ፡ ተስፋ ፡ ሰጣትና [3]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

ወንድምንም ፡ አየሁት ፡ ጉድጓድ ፡ ሲጥል
ለባርነትም ፡ ሲሸጥ ፡ ለባዕድ ፡ ወገን [4]
ጌታ ፡ ግን ፡ ከግዞት ፡ አወጣውና
በረከት ፡ ሆነ ፡ ዮሴፍ ፡ ነገሠና [5]

ከሞተ ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ሆኖታል
አለችው ፡ እህቱ ፡ አሁንስ ፡ ሸቶአል
የኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ መቸ ፡ ያሸተዋል
አላዛርን ፡ በድንቅ ፡ ከሞት ፡ ያስነሳዋል [6]

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

እዮብ ፡ በቁስል ፡ እጅግ ፡ ተመቶ
ሚስቱ ፡ እንኳን ፡ ጠልታው ፡ የሚቀርበው ፡ አጥቶ
ክደህ ፡ ሙት ፡ ብላ ፡ ስታስቸግረው
በሸክሙ ፡ ላይ ፡ ቀንበር ፡ ስትጭነው [7]
አምላኩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከተፍ ፡ አለለት
ምርኮውን ፡ በእጥፍ ፡ በእጥፍ ፡ መለሰለት [8]
ሁሉንም ፡ በተራው ፡ አየሁት ፡ ቃኘሁት
ግን ፡ ኢየሱሴን ፡ በልጦ ፡ አገኘሁት

አዝ፦ ለእኔስ ፡ አዳኜ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ
የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የእውነት ፡ የእውነት
የእውነት ፡ አፍቃሪዬ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue