Meserete Kirstos Choir--Endet Dink Amlak New--Ke Mekaber Wodia (ከመቃብር ፡ በላይ)

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ወዲያ ፡ ማን ፡ ይከተለኛል
ዝናም ፡ ይከዳኛል ፡ ሃብትም ፡ ይተወኛል ፡ ጊዜም ፡ ይረሳኛል
ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ያዋጣናል

ሃብቴም ፡ አሁን ፡ ያልፋል
ቁመናም ፡ እንድ ፡ ቀን ፡ ይጥለኛል
ሁሉም ፡ ይጥላል
የጌታዬ ፡ ዝና ፡ ዘላቂ ፡ ነውና
ፍቅር ፡ ባለዝና
ከመቃብር ፡ ወዲያ ፡ መጠለያ (፪x)

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ወዲያ ፡ ማን ፡ ይከተለኛል
ዝናም ፡ ይከዳኛል ፡ ሃብትም ፡ ይተወኛል ፡ ጊዜም ፡ ይረሳኛል
ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ያዋጣናል

እውነትን ፡ አውቂ ፡ ጥበበኛ
ወይም ፡ ድሃ ፡ ብሆን ፡ ችግረኛ
ዝናዬ ፡ ነው፡ የሚያልፈኝ
ሆኘ ፡ በዚህ ፡ ብገኝ
ከሞት ፡ ወዲህ ፡ ወዲያ
ካለአምላኬ ፡ ዝና
የላትማ ፡ በዚያ ፡ ነፍሴ ፡ መጠለያ (፪x)

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ወዲያ ፡ ማን ፡ ይከተለኛል
ዝናም ፡ ይከዳኛል ፡ ሃብትም ፡ ይተወኛል ፡ ጊዜም ፡ ይረሳኛል
ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ያዋጣናል

ከሞት ፡ ወዲያ ፡ ማዶ ፡ ድል ፡ አድራጊ
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው ፡ ታዳጊ
በሞት ፡ ጣል ፡ ሼድ ፡ አንድም ፡ ነገር ፡ አልያዝኩኝም
ሁሉን ፡ ነገር ፡ ትቻለሁ ፡ በእየሱስ ፡ አርፋለሁ (፪x)

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ወዲያ ፡ ማን ፡ ይከተለኛል
ዝናም ፡ ይከዳኛል ፡ ሃብትም ፡ ይተወኛል ፡ ጊዜም ፡ ይረሳኛል
ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ያዋጣናል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue