Lebego New (ለበጐ ፡ ነው )

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን
ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x)
እናመሰግናለን (፪x)

እርሱ ፡ አይሳሳትም ፡ ሁልጊዜ ፡ ልክ ፡ ነው
ደግሞም ፡ የሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው
የእኛ ፡ ሃሳብ ፡ ካልሆነ ፡ ይቅር ፡ ምሬታችን
የያዝነውን ፡ ጌታ ፡ መጠራጠራችን (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን
ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x)
እናመሰግናለን

የፀሎት ፡ መልስ ፡ ቢዘገይ ፡ ቢሆንም ፡ ዝምታ
ብዙ ፡ ጥያቄዬ ፡ እንኳን ፡ መልስ ፡ ቢያጣ
የጠራኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ አምነዋለሁ
ስንቱን ፡ አሳልፎኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን
ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x)
እናመሰግናለን

በለሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል
ጌታውን ፡ የሚጠብቅ ፡ ደግሞ ፡ ይከብራል
ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ እመሰክራለሁ
እናንተም ፡ እመኑት ፡ ደግሜ ፡ እላለሁ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩት
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን
ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x)
እናመሰግናለን

የሚያልፍ ፡ ባይመስልም ፡ በዝቶ ፡ ችግራችን
የራቀ ፡ ቢመስልም ፡ጌታ፡ ከጐናችን
ቆመን ፡ እንጠብቀው ፡ በመጠበቂያችን
ተስፋውን ፡ የሰጠን ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታችን (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩት
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን
ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x)
እናመሰግናለን

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue