Meqaberun Feneqaqelew (መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው)

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

መቃብር ፡ ሊያዘው ፡ አልቻለም
ጌታችን ፡ ተቀብሮ ፡ አልቀረም
ጐልጐታ ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ የነበረው
መቅብሩን ፡ ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

ከሙታን ፡ መካከል ፡ ሕያውን
የምትፈልጉት ፡ አረ ፡ ለምን
እዚህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነስቷል
መቃብሩን ፡ ባዶ ፡ አድርጐታል
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

ወታደር ፡ ሲጠብቅ ፡ የቄሳር
ኢየሱስን ፡ ሊያስቀር ፡ መቃብር
ከኃይል ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ኃይል ፡ ያለው
መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

እንደ ፡ ሰው ፡ የሞተው ፡ ያ ፡ ጌታ
በድካሙ ፡ ጠላት ፡ የረታ
የሞትንም ፡ ጉልበት ፡ ሰባብሮ
ድል ፡ አድርጓል ፡ ማህተሙን ፡ ሽሮ
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

መድኃኒት ፡ ከጽዮን ፡ የወጣ
ሊያድነን ፡ ከሰማይ ፡ የመጣ
ሞትን ፡ ለዘለዓለም ፡ የሻረው
መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ

አዝ፦ መቃብሩን ፡ ፈነቃቀለው (፪x)
ተነሳ (፫x) ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x)

Baru-baru ini Didengarkan oleh

0 komentar
    Tidak ada komentar yang ditemukan

:: / ::
::
/ ::

Antre