Nefsien Befitih (ነፍሴን ፡ በፊትህ )

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

ሊታይ ፡ በማይችል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ አለህ
ሠማይ ፡ ምድርን ፡ በቃል ፡ ታዛለህ
ወደደም ፡ ጠላም ፡ ፍጥረት ፡ በሙሉ
ይገዛልሃል ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ኃይሉ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

ሰው ፡ ህልውናው ፡ ሞትና ፡ ሕይወቱ
ሃዘን ፡ ደስታው ፡ ሹመት ፡ ሽረቱ
ትእዛዝ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ይወጣል
ክብር ፡ ላንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል?

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

እስከ ፡ እግርህ ፡ ጣት ፡ ዕንቁ ፡ ለብሰሃል
ወገብህንም ፡ በወርቅ ፡ ታጥቀሃል
ራስህ ፡ ነጭ ፡ ነው ፡ ዐይንህ ፡ ነበልባል
ክብርም ፡ ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ይገባል

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

እግርህ ፡ በእቶን ፡ የነጠረ ፡ ናስ
ድምፅህ ፡ ያስፈራል ፡ እንደ ፡ ውቅያኖስ
የተሳለ ፡ ሰይፍ ፡ ከአፍህ ፡ ይወጣል
ከቀትር ፡ ፀሐይ ፡ ፊትህ ፡ ያበራል

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

ውለታህ ፡ በዝቶ ፡ ቢያስጨንቀኝ
ያለኝን ፡ ሸጬ ፡ ሽቶ ፡ ገዛሁኝ
ብልቃጡ ፡ ይሰበር ፡ ይፍሰስ ፡ በእግርህ
እንዳከበርከኝ ፡ እኔም ፡ ላክብርህ

አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ
እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ
ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ
ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ
አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ
ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

:: / ::
::
/ ::

대기줄