Bekeraniyo Yaderegelign (በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ)

ስለት ፡ ነበረብኝ ፡ ለኢየሱስ ፡ ለጌታ
እንዲህ ፡ ካረገልኝ ፡ እስራቴን ፡ ከፈታ
እንደመልካም ፡ አባት ፡ አንጀቱ ፡ ራርቶ
አይዞህ ፡ ልጄ ፡ አለኝ ፡ ሳልጮህ ፡ ገና ፡ ሰምቶ (፪x)

ሃጥያት ፡ እየሰራሁ ፡ እንዲያ ፡ እያደከምኩት
የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩን ፡ እየዘነጋሁት
ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ግን ፡ ይከታተሉኛል
አባብለው ፡ አምጥተው ፡ ቤቱ ፡ ያገቡኛል
ፊቱ ፡ ያቆሙኛል

አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ

ከአቻምና ፡ አምና ፡ ከአምና ፡ ዘንድሮ
የጌታ ፡ ውለታ ፡ አያልቅም ፡ ተቆጥሮ
የምህረቱ ፡ ብዛት ፡ የፍቅር ፡ ጥልቀቱ
ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገባ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ
የጌታ ፡ ምህረቱ

የፍቅር ፡ ዓይኖቹን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያቀና
በምክር ፡ እግሮቹን ፡ ወደኔ ፡ ያቀና
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ባርኮኛልና
ይኸው ፡ መስዋእቴ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና
ከልቤ ፡ ምሥጋና

አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ

የሚያስጨንቀኝን ፡ ከሳሼን ፡ አዋርዶ
ሳልመርጠው ፡ የመረጠኝ ፡ ሳልወደው ፡ እጅግ ፡ ወዶ
ከአባቱ ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ የሚያዘጋጅልኝ
ባለውለታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ይክበርልኝ
ጌታ ፡ ይክበርልኝ

ከአጥናፍ ፡ እስከ ፡ አጥናፍ ፡ ጌታን ፡ አክብሩክኝ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ በሉ ፡ ዘምሩልኝ
የጌታ ፡ ውለታ ፡ መግለጫ ፡ ያላችሁ
እስኪ ፡ እናምልከው ፡ ዕልል ፡ እያላችሁ
ክበር ፡ እያላችሁ

አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ (፪x)

እስኪ ፡ ቆም ፡ ብላችሁ ፡ አስቡ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ
እናንተን ፡ ለማዳን ፡ ስለሞተው ፡ ጌታ
በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ የተንጠለጠለው
ከዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አንተን ፡ ለማዳን ፡ ነው
አንቺን/እኛን ፡ ለማዳን ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue