ክቡር ፡ ነው

በአንተ ፡ የተደነቀ ፡ ምህረት ፡ የበዛለት
ምስግናን ፡ ያመጣል ፡ ፍቅሩን ፡ ሊገልጽበት
ዘመኑን ፡ በሙሉ ፡ ቢቀኙ ፡ ለክብርህ
ከመታወቅ ፡ ያልፋል ፡ የአንተስ ፡ ማንንነት

ዝማሬው ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት
ምሥጋናው ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት
አድንቆት ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት
የቱም ፡ አይገልጸዉ ፡ የእርሱን ፡ የእርሱን ፡ ታላቅነት
የቱም ፡ አይገልጸዉ ፡ የእርሱን ፡ ኃያልነት

ክቡር ፡ ነው ፡ የከበረ ፡ በክብር ፡ የተሞላ
ድንቅ ፡ ነው ፡ የሚደነቅ ፡ በኃይል ፡ በሥራ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ የሚወደድ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚፈራ
እግዚአብሔር ፡ የሚደነቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚያኮራ

አምላኬ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ዝማሬ ፡ ይገልጽሃል (፪x)
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ምሥጋና ፡ ይገልጽሃል (፪x)
አባቴ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ምሥጋና ፡ ይገልጽሃል (፪x)

ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፬x)

ላስተዋለውማ ፡ ሆሆ ፡ ፀጋው ፡ ለበዛለት
ንቆ ፡ ይህን ፡ ዓለም ፡ አሃ ፡ የሚጠፋውን ፡ እውነት
በእምነት ፡ እያየው ፡ ፊትህን ፡ እለት ፡ እለት ፡ ኦሆ
እንዴት ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ ለክብርህ ፡ መቀኘት (፪x)

ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፬x)

ክቡር ፡ ነው ፡ የከበረ ፡ በክብር ፡ የተሞላ
ድንቅ ፡ ነው ፡ የሚደነቅ ፡ በኃይል ፡ በሥራ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ የሚወደድ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚፈራ
እግዚአብሔር ፡ የሚደነቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚያኮራ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue