Endih Yarekelegn (እንዲህ ፡ ያረክልኝ )

አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር
እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x)

የሚያውቅህ ፡ ነው ፡ የሚያውቀው
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ የገባው
እህል ፡ ውሃ ፡ ማያሰኘው
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አያምረው (፪x)

አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር
እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x)

ያየሁትን ፡ አይቼ ፡ ነው
እንዲህ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ ፡ ምዘምረው
ሊካድ ፡ የማይቻል ፡ እውነትህ
ማርኮ ፡ አስቀርቶኛል ፡ ያ ፡ ፍቅርህ (፪x)

አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር
እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x)

ዝም ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ያስችለኛል
የእግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ይለኛል
ለቀየረው ፡ ለርሱ ፡ የኔን ፡ ሕይወት
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምነው ፡ በሆንኩለት (፪x)

አዝ:- ግዑዝ ፡ እንኳን ፡ ያመልክሃል ፡ የማያውቅህ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር
እንኳን ፡ ቀምሶ ፡ ያጣጣመህ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ አይነት ፡ ፍጡር (፫x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue