Yeadis Kidan Beg(የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ).mp3

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የጽድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድህን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በላይ ፡ በሰማይ (፪x)

ከብዶ ፡ የነበረው ፡ የህግ ፡ ጭነት
ፍጥረትን ፡ ሲያስጨንቅ ፡ ስለ ፡ ኀጢአት
የህዝብን ፡ ኀጢአት ፡ አንዴ ፡ ለማስጠረግ
ኢየሱስ ፡ ጣቱን ፡ ሰጠ ፡ ለመስቀል ፡ ስቅላት

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የጽድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድህን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በላይ ፡ በሰማይ (፪x)

የሃጥያት ፡ መጋረጃ ፡ እኛን ፡ የለየንን
ኢየሱስ ፡ ተረተረው ፡ መስዋዕት ፡ ሆኖልን
ቅድስተ ፡ ቅዱሳን ፡ የተስፋው ፡ ሃገር
በእርሱ ፡ ልንገባ ፡ ቻልን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ በር

የኮርማ ፡ ደም ፡ መሥዋዕት ፡ ለእኛ ፡ አያስፈልገንም
አንዴ ፡ ተረጭተናል ፡ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም
ቅዱስ ፡ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ መካከለኛ
ነፍሱን ፡ ወዶ ፡ ሰጠ ፡ ለሞት ፡ ለእኛ

አዝ፦ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ቅዱስ ፡ ካህን
የጽድቅ ፡ ንጉሥ ፡ የዓለም ፡ መድህን
የእውነተኛይቱ ፡ ድንኳን ፡ አገልጋይ
ቅዱስ ፡ ካህን ፡ አለን ፡ በላይ ፡ በሰማይ (፪x)

Recently Listened by

1 comments

:: / ::
::
/ ::

Queue