Yanebesane Afe Yezega (የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ)

አዝ፦ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ ፡ ጠላቴንም ፡ የወጋ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ከትውልዱ ፡ ወሰን ፡ እኩያ ፡ የሌለው
ፊተኛው ፡ ኋለኛው ፡ ዘላለም ፡ የሆነው
የዕውቀት ፡ ማህደር ፡ የሰላም ፡ አለቃ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ የነፍሴ ፡ ጠበቃ

አዝ፦ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ ፡ ጠላቴንም ፡ የወጋ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ፍርሃትን ፡ ከቦ ፡ ችግር ፡ ሲጋርደኝ
አንበሳው ፡ አፍጦ ፡ ሊገለባብጠኝ
ደረሰ ፡ ጌታዬ ፡ የአማልክቶች ፡ አምላክ
ይኸው ፡ ነፃ ፡ ወጣሁ ፡ አምልኬ ፡ ይባረክ

አዝ፦ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ ፡ ጠላቴንም ፡ የወጋ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ዘመን ፡ የማይሸረው ፡ የዘመናት ፡ ጌታ
ሞትንም ፡ ድል ፡ ነስቶ ፡ ሲኦልን ፡ የረታ
ኃያል ፡ የሆነ ፡ ድንቅ ፡ ምርኮን ፡ የሚያመጣ
ለእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አቻ ፡ ከየት ፡ መጣ

አዝ፦ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ ፡ ጠላቴንም ፡ የወጋ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ፍሙን ፡ አጋግሎ ፡ አሳቱን ፡ አንድዶ
ሊያጠፋኝ ፡ ሲፈልግ ፡ ያ ፡ ቸካኙ ፡ ዘንዶ
ቃል ፡ ኪዳን ፡ የገባው ፡ ደረሰ ፡ ጌታዬ
በረታሁ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ ተድሶ ፡ ተስፋዬ

አዝ፦ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ የዘጋ ፡ ጠላቴንም ፡ የወጋ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue