Alage Lante Misgana (አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና)

አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x)

ገና ፡ በልጅነት ፡ በልጅነት ፡ ስለለመድኩኝ
ውለታህን ፡ እያሰብ ፡ እያሰብ ፡ አመሰገንኩኝ
አሁን ፡ የምሥጋና ፡ ጥቅሙ ፡ ኃይሉ ፡ ሲገባኝ
ከነገሬ ፡ በፊት ፡ አስቀድሜ ፡ አመሰገንኩኝ
ምሥጋና ፡ ሲቀድም ፡ ሲወጣ ፡ ሲሆን ፡ መጀመሪያ
አውቃለሁ ፡ በረከት ፡ . (1) . ፡ ፈጥኖ ፡ ለእኔ ፡ እንደሚመጣ

አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x)

ጠብቄ ፡ ጥያቄዬ ፡ ጥያቄዬ ፡ ሲመለስልኝ
ምሥጋና ፡ ለአምላኬ ፡ ለአምላክ ፡ ሠጥ ፡ ቆየሁኝ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ሲገባኝ ፡ ሲገባኝ ፡ ሲገለጥ ፡ ነገሩ
በልጅ ፡ አንደበቴ ፡ አንደበት ፡ ምሥጋና ፡ ማኖሩ
ጠላት ፡ ምቀኛዬ ፡ ምቀኛዬ ፡ ለማጥፋት ፡ ነው ፡ ለካ
ስለዚህ ፡ ላመስግን ፡ ላመስግነው ፡ በምንም ፡ ሁኔታ

አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x)

ከፊቴ ፡ የቆመው ፡ ተራራ ፡ አይደለውም ፡ መናዱ
ከሰማይም ፡ መና ፡ ወይም ፡ ሥጋ ፡ አይደለም ፡ መውረዱ
ተራራው ፡ ሳይናድ ፡ ሳይናድ ፡ መናው ፡ ሳይወርድልኝ
ይሁዳን ፡ ከፊቴ ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድማለሁኝ
ምሥጋና ፡ ሲቀድም ፡ ሲወጣ ፡ ሲሆን ፡ መጀመሪያ
አውቃለሁ ፡ በረከት ፡ . (2) . ፡ ፈጥኖ ፡ ለእኔ ፡ እንደሚመጣ

አዝ:- ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
ከውስጤ ፡ የሚፈልቅ ፡ ከልብ ፡ የሚወጣ
አለኝ ፡ አለኝ ፡ አለኝ ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue