Kiber Medhanite (ክበር ፡ መድሃኒቴ)

አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም
ድምፅህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ
በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ (፪x)

ልባችን ፡ ሲዝል ፡ ሲደነድን
አለህ ፡ ማድቀቁያ ፡ መዶሻ ፡ ቃል
ለደረቀ ፡ አጥንት ፡ ሕይወት ፡ ይሰጣል
ታላቅ ፡ ሰራዊት ፡ አርጐ ፡ ያቆማል

አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም
ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ
በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ

ዛፍ ፡ ስር ፡ ስንወድቅ ፡ አይሎ ፡ ሰልፍ
የስንፍናን ፡ ቃል ፡ ስንለፈልፍ
ትከሻህ ፡ አይዝል ፡ ፊትህ ፡ አይጠቁርም
የወደድከውን ፡ ሰውን ፡ አትጥልም

አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም
ቃልህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ
በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ

ቃልህ ፡ ጅማትን ፡ ቅልጥም ፡ ይወጋል
ነፍስንና ፡ መንፈስንም ፡ ይለያል
በምክሩም ፡ ግሩም ፡ ጣፋች ፡ ሲበላ
እንከን ፡ የሌለው ፡ የማር ፡ ወለላ

አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም
ጌታያ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም
ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ
በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ

ኢየሱስ ፡ በቃሉ ፡ የፈወሳችሁ
በቅዱስ ፡ መንፈሱ ፡ የነካካችሁ
እንደኔ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ያላችሁ
አክብሩት ፡ ጌታን ፡ እልል ፡ ብላችሁ

አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም
ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ
በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue