Tsion Hoy Teneshi (ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ)

የምሬት ፡ ጊዜ ፡ የአምባ ፡ ጊዜሽ
ያንን ፡ መከራ ፡ ጉስቁልናሽ
ተመልክቶታል ፡ በቃ ፡ አታልቅሺ
ዘምሪ ፡ ዕልል ፡ በይ ፡ ጽዮን ፡ ተነሺ (፪x)
ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ

አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ
ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ
አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ

የእግዚአብሄር ፡ ጆሮዎች ፡ ጸሎትሽን ፡ ሰምተዋል
አንቺን ፡ ለማዳን ፡ እጁን ፡ ዘርግቷል
ያንን ፡ መከራ ፡ የሚያስረሳሽ
ይዞልሽ ፡ መጥቷል ፡ ድንቅ ፡ በረከቱን (፪x)

አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ
ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ
አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ

ትላንት ፡ በለቅሶ ፡ ለዘራሺው ፡ ዘርሽ
መጥቶልሻል ፡ ጌታ ፡ በሳቅ ፡ ሊያሳጭድሽ
ያኔ ፡ በመከራሽ ፡ የገባልሽን ፡ ቃል
ጌታ ፡ ሊፈጽመው ፡ ከማደሪያው ፡ ነቅቷል (፪x)

አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ
ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ
አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue