Amnihalehu Geta (አምንሃለሁ ፡ ጌታ)

አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x)
ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x)
አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x)

ጨለማው ፡ እጅግ ፡ በርትቶ
ተስፋ ፡ የሚጣልበት ፡ ጠፍቶ
ግራ ፡ ቀኝ ፡ በሩ ፡ ሲዘጋ
ተጣራሁ ፡ ረዳት ፡ ፍለጋ

ጩኸቴን ፡ ሰምተህ ፡ ከሰማይ
ወርደሃል ፡ በጠላቴ ፡ ላይ
ወጀቡን ፡ ጸጥ ፡ አረክልኝ
ኢየሱስ ፡ ጋሻ ፡ ሆንክልኝ (፪x)

አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x)
ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x)

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድሃኒት
ኢየሱስ ፡ ድንቅ ፡ የሰራኅልኝ
ኢየሱስ ፡ ተራራውን ፡ ንደህ
ኢየሱስ ፡ ሜዳ ፡ አደረክልኝ
ኧረ ፡ አይቻልም ፡ ከእንግዲህስ ፡ አልልም
በዐይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ አልጠራጠርም
አንተ ፡ ይሁን ፡ ካልክ ፡ የማይሆን ፡ ይሆናል
ወደደም ፡ ጠላም ፡ ፍጥረት ፡ ይሰማሃል
ጌታ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማን ፡ ይቃወምሃል
ባሕሩን ፡ ስትከፍለው ፡ ዐይኖች ፡ አይተውሃል
ጌታ ፡ ነህ (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ ይቃወምሃል
ባሕሩን ፡ ስትከፍለው ፡ ዐይኖች ፡ አይተውሃል

አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x)
ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x)
አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x)
ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x)

האזינו לאחרונה על ידי

0 הערות
    לא נמצאו הערות

:: / ::
::
/ ::

תוֹר