Kelellegne (ከለለኝ)

አዝ:- ከለለኝ (፮x)
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ (፪x)

ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ
(አሃ ፡ አሃ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ)
ከግራና ፡ ከቀኝ ፡ የሚረዳኝ ፡ ጠፍቶ
(አሃ ፡ አሃ ፡ የሚረዳኝ ፡ ጠፍቶ)
ወደ ፡ ተራሮች ፡ ላይ ፡ ዓይኖቼን ፡ ባነሳ
(አሃ ፡ አሃ ፡ ዓይኖቼን ፡ ባነሳ)
ረዳት ፡ ከወዴት ፡ ይምጣ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳኝ
(አሃ ፡ አሃ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳኝ)

የማይረሳ ፡ አምላክ ፡ ድንገት ፡ ያስባል
ምስክሩ ፡ ነኝ ፡ እኔን ፡ ረድቶኛል
ሰማይን ፡ ቀዶ ፡ ወርዶ ፡ አሳረፈኝ
አባት ፡ አለኝ ፡ ልበል ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ አይለኝ (፪x)

አዝ:- ከለለኝ (፮x)
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ

ቀድሞኝ ፡ እየወጣ ፡ ከፊት ፡ ፊት ፡ ሲመራኝ
(አሃ ፡ አሃ ፡ ከፊት ፡ ፊት ፡ ሲመራኝ)
አልረሳም ፡ ካችሃምና ፡ እንዴት ፡ እንደረዳኝ
(አሃ ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ እንደረዳኝ)
እንደ ፡ ዐይኖቹ ፡ ብሌን ፡ ተተንቅቆልኛል
(አሃ ፡ አሃ ፡ ተጠንቅቆልኛል)
አፌን ፡ ሞልቼ ፡ ልበል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያድናል
(አሃ ፡ አሃ ፡ አምላኬ ፡ ያድናል)

ውዴን ፡ ተደግፌ ፡ ወጣሁ ፡ ከበረሃ
ዙሪያዬን ፡ አጠረው ፡ ደስታና ፡ ፍሰሃ
የማምለጫ ፡ አለት ፡ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆኖኛል
ጥበቃውን ፡ ሳስብ ፡ ዘምር ፡ ያሰኘኛል (፪x)

አዝ:- ከለለኝ (፮x)
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ
ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት
ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue