Kristian Teshagere (ክርስቲያን ፡ ተሻገረ)

አብን ፡ በዙፋኑ ፡ ወልድን ፡ በስተቀኙ
በምድር ፡ የተገፋውን ፡ በክብር ፡ ሊገናኙ
ሲጋብዙት ፡ ታይቶት ፡ ክርስቲያን ፡ በጣሩ
ተፈፀመ ፡ ብሎ ፡ ወጣ ፡ ከሃሩሩ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

እውር ፡ ፈሪሳውያን ፡ በምናቸው ፡ ይዩ
ፀዳል ፡ መፈንጠቁን ፡ ከችግር ፡ ትይዩ
በመከራ ፡ ናዳ ፡ በሰዎች ፡ ጫጫታ
ሩጫውን ፡ አከተመ ፡ ጀግናው ፡ ሳይረታ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

ሃገር ፡ ሃገር ፡ ሲዞር ፡ ሲንከራተት ፡ ከርሞ
መልኩ ፡ ተቀይሮ ፡ በመከራ ፡ ከስሞ
ከጅራፍ ፡ ከዱላ ፡ ከጨካኞች ፡ ጡጫ
ክርስቲያን ፡ አንቀላፋ ፡ አረፈ ፡ ከእርግጫ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

እንደነ ፡ ያዕቆብ ፡ በደም ፡ ተበክለዉ
ለወንጌል ፡ ሊደፉ ፡ ለቃልኪዳናቸው
በሰልፍ ፡ ቆመዋል ፡ ተራ ፡ ይጠብቃሉ
ኢየሱስ (፫x) ፡ ይላሉ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue