Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--ፍቅርህ ፡ መልካም ፡ ነው

ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅርህ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)
አመልክሃለሁ ፡ በቀንም ፡ በሌሊትም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ (፪x)

የህይወቴ ፡ ጌታ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ
የሕይወቴ ፡ ተስፋ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም
ከአንተ ፡ ውጬ ፡ ሌላ ፡ የለም ፡ አዎ ፡ ሌላ ፡ የለም
አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፡ አዎ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

እስከዛሬ ፡ ስኖር ፡ በዚህች ፡ ምድር
አንድም ፡ አላየሁም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)
ሁሉ ፡ ሲይዙት ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ ሲጨብጡት ፡ እንደ ፡ ጉም ፡ ነው
ኢየሱስ/ጌታ ፡ በአንተ ፡ ማረፍ ፡ ግን ፡ እጅግ ፡ መታደል ፡ ነው (፪x)

እገባለሁ ፡ ወደውስጥ ፡ አንተ ፡ ወዳለህበት
እመጣለሁ ፡ በደስታ ፡ ለአንተ ፡ ልገዛ ፡ ጌታ
እገባለሁ ፡ ወደውስጥ ፡ አንተ ፡ ወዳለህበት (ወዳለህበት)
እመጣለሁ ፡ በደስታ ፡ ለአንተ ፡ ልገዛ ፡ ጌታ (እየሰገድኩ)

እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (ለአንተ ፡ እገዛለሁ) ለአንተ ፡ እገዛለሁ
እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) ፡ እያመለኩ ፡ (አንተን ፡ አነግሳለሁ) አንተን ፡ አነግሳለሁ
እየሰገድኩ (ጌታዬ) ፡ እያመለኩ (ለአንተ ፡ እኖራለሁ) ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ
እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (አንተን ፡ አንተን) አንተን ፡ አከብራለሁ
እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ (ለአንተ ፡ እገዛለሁ) ለአንተ ፡ እገዛለሁ
እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) ፡ እያመለኩ ፡ (ጌታ ፡ አነግሻለሁ) አንተን ፡ አነግሳለሁ
እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue