Baskemetkegn Bota (ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ)

በእምነት ፡ መኖሪያዬን ፡ ሰርተህ ፡ ውብ ፡ አድርገህ
ምግብን ፡ ያለ ፡ ድካም ፡ እንድበላ ፡ ብለህ
ያስቀመጥክኝን ፡ ሰው ፡ ወረት ፡ ሲደልለኝ
እጦት ፡ ሲያራቁተኝ ፡ በቸልታ ፡ አትየኝ

አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ

ልቤ ፡ እየቸኮለ ፡ እግሬ ፡ ሮጥ ፡ እያለ
ውርደትን ፡ ለማየት ፡ ዓይኔ ፡ እየከጀለ
ድንበር ፡ እየጣሰ ፡ ከኃጢአት ፡ እየዋለ
የማታ ፡ የማታም ፡ ሚዛኔ ፡ ቀለለ

አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ

የጭንጫ ፡ ቡቃያ ፡ ፈጥኖ ፡ እየበቀለ
ፀሐይ ፡ ስትወጣ ፡ ነዶ ፡ ተቃጠለ
አንተን ፡ ሆኜ : እኔ ፡ ፍሬን ፡ እንዳፈራ
አንስተህ ፡ አትጣለኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አደራ

አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ

ቸኮል ፡ ያለ ፡ ሳዖል ፡ በዓይኖችህ ፡ ተንቆ
ብላቴናው ፡ ዳዊት ፡ ተቀብቷል ፡ ልቆ
ዓይኔን ፡ ግለጠውና ፡ ስፍራዬ ፡ ልወቀው
አሳድገኝ ፡ እንጂ ፡ ዕድሜዬን ፡ አትቁረጠው

አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ

حال ہی میں سنا

0 تبصرے
    کوئی تبصرہ نہیں ملا

:: / ::
::
/ ::

قطار