Ruth Tadesse Ekedisehalew

አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ
በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x)

ድሮ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፊት ፡ ገና ፡ ያኔ
መስዋእቴን ፡ ለካህንህ ፡ ስሰጥ ፡ እኔ ፡ ውጭ ፡ ቆሜ
ካህኑ ፡ የገባው ፡ እየቀደሰህ
እኔም ፡ እመኝ ፡ ነበር ፡ ክብርህን ፡ ማየት
ዛሬማ ፡ ሆነልኝ ፡ እኔም ፡ በልጅህ
ደፍሬ ፡ እንድገባ ፡ ወደ ፡ መገኛህ

አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ
በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x)

ብዙዎች ፡ ያመልካሉ ፡ ስለማያውቁት
ስፍራን ፡ ይመርጣሉ ፡ ለማቅረብ ፡ ለአንተ ፡ ስግደት
እኔ ፡ ግን ፡ እያወኩ ፡ ገብቶኝ ፡ ማንነትህ
በመንፈስ ፡ በእውነት ፡ ወደድኩኝ ፡ ላመልክህ
ካህን ፡ አልፈልግም ፡ ረዳትስ ፡ ለእኔ
እቀድስሃለሁ ፡ ብቻዬን ፡ መጥቼ

አዝ:- እቀድስሃለው ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኬ
በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x)

መስዋእት ፡ አለ ፡ ከኔ ፡ ለአንተ ፡ ምሰጥህ
ስለ ፡ አደረክልኝ ፡ አይደል ፡ ገብቶኝ ፡ እንጂ ፡ ማንነትህ
በግሌ ፡ አወቅኩህ ፡ ወደድኩህ ፡ ከልቤ
በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬ
በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ አዳኜ ፡ ነህ ፡ ብዬ
በማወቅ ፡ ተናገርሁ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ብዬ

አዝ:- እቀድስሃለው (፫x) ፡ ጌታዬ
በውጪ ፡ አይደለም ፡ ማደሪያህ ፡ ገብቼ ፡ ገብቼ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue