Qirbe Neh (ቅርቤ ፡ ነህ)

ሰማያትን ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ እንደማይ
ሳየውም ፡ ሩቅ ፡ እንደሆነ
አምላኬ ፡ እንደእዛ ፡ አላይህም
እግዚአብሔር ፡ እንደእዛ ፡ አላርቅህም

ቅርብ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አለህ ፡ አጠገቤ (፬x)

ሰማይ ፡ ሰፋህ ፡ አልለው ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ
ግን ፡ መረጥክ ፡ ልትገባ ፡ ልትቆይ ፡ ከልቤ
የታሰበ ፡ ኧረ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ የተዘጋጀ
ስለዚህ ፡ አውቃለሁ ፡ አጠገቤ ፡ እንዳለህ

አዝ:- ቅርቤ ፡ ነህ ፡ ከጐኔ ፡ ነህ (፪x)
ይሰማኛል ፡ ህልውናህ (፪x)

የጠየኳቸው ፡ ጥያቄዎች ፡ ሁሉ
መልስን ፡ ብትሰጣቸው ፡ ወይም ፡ ቢዘገዩ
እነሱንም ፡ አይቼ ፡ ቅርቤ ፡ አላልኩህም
እስከ ፡ ፍጻሜ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አመንኩት ፡ ቃልህን

አዝ:- ቅርቤ ፡ ነህ ፡ ከጐኔ ፡ ነህ (፪x)
ይሰማኛል ፡ ህልውናህ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue