Telate Hoy (ጠላቴ ፡ ሆይ)

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

የወይኑ ፡ ፍሬ ፡ ተለቅሞ ፡ እንደቀረው ፡ ቃርሚያ
ደርቄ ፡ ቆሜያለሁ ፡ እኔ ፡ ከበረከት ፡ በስቲያ
የሃዘን ፡ እንጉርጉሮዬን ፡ የምሬት ፡ ለቅሶዬን
በአምላኬ ፡ ፊት ፡ እለቃለሁ ፡ እንዲያያት ፡ ሕይወቴን

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

በእግዚአብሔር ፡ ላይ ፡ ኃጥያትን ፡ ሰርቻለሁና
ቁጣው ፡ ለክፋቴ ፡ ሆኖ ፡ ነዶብኛልና
ወደ ፡ ብርሃን ፡ እስኪያወጣኝ ፡ እታገሳለሁኝ
ከውስጡም ፡ እስኪምረኝ ፡ ድረሰ ፡ ጠብቀዋለሁኝ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

በእኔና ፡ በአምላኬ ፡ መሃል ፡ የሚኖረውን ፡ ጉዳይ
ኢየሱስ ፡ ይፈፅመዋል ፡ የመሰረቱ ፡ ድንጋይ
ስለዚህ ፡ ጠላቴ ፡ ወግድ ፡ ጌታ ፡ ይገስጽህ
አሁንም ፡ ቢሆን ፡ ልጁ ፡ ነኝ ፡ ተረዳ ፡ ከልብህ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

ለዘለዓለም ፡ አይቆጣም ፡ ምህረትን ፡ ይወዳል
የጠላቴን ፡ ምኞት ፡ ቆርጦ ፡ ደስታውን ፡ ያቆማል
የውርደት ፡ ማቄ ፡ ተቀዶ ፡ ነጭ ፡ ልብስ ፡ ለብሼ
ዳግም ፡ ዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ ክንዱን ፡ ተንተርሼ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን
እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue