• 250
  • 0
  • 0
  • 1
  • 0

Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--አመልክሃለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

በሰማይ ፡ አየሁ ፡ አንተን ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
በምድርም ፡ አየሁ ፡ አንተን ፡ የሚመስልህ ፡ የለም
ከምድር ፡ በታችም ፡ አየሁ ፡ አንተን ፡ የሚመስልህ ፡ የለም

በልጠህብኛልና ፡ መርጬሃለሁ
ተሽለኸኛልና ፡ ተከትዬሃለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
ለአንተ ፡ እገዛለሁ (፬x)

አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አመልክሃለሁ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ
እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
ለእኔ ፡ የሚበጅ (፪x)
አንተን ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ አመልካለሁ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ ፡ እገዛለሁ
ከአንተ ፡ ውጬ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ የለኝም (፬x)

ከማን ፡ ጋር ፡ አንተን ፡ ጌታ ፡ አስተካክላለሁ
ከምን ፡ ጋር ፡ አንተን ፡ ኢየሱስ ፡ አመሳስላለሁ
ከየትኛውስ ፡ ጋራ ፡ አንተን ፡ አወዳድራለሁ

ከብርና ፡ ከወርቅ ፡ ፍቅርህ ፡ በልጦብኛል
ከሃጣን ፡ ድንኳን ፡ ይልቅ ፡ ቤትህ ፡ ተሽሎኛል
ወደአንተ ፡ መጠጋቴ ፡ ለእኔስ ፡ በጅቶኛል (፬x)

አዝ፦ አመልክሃለሁ (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አመልክሃለሁ (የእኔ ፡ ወዳጅ) ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (የእኔ ፡ ወዳጅ)
እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
ለእኔ ፡ የሚበጅ (፬x)
አንተን ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ አመልካለሁ
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ ፡ እገዛለሁ
ከአንተ ፡ ውጬ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ የለኝም (፰x)

Baru-baru ini Didengarkan oleh

0 komentar
    Tidak ada komentar yang ditemukan

:: / ::
::
/ ::

Antre