Ye Yesus Sime (የኢየሱስ ፡ ሥም)

ከጠላቴ ፡ ጋራ ፡ ስሟገት
ነፍሴም ፡ አታ ፡ ሳለ ፡ እረፍት
ወደ ፡ ተራሮችም ፡ አየሁ
እረዳት ፡ ግን ፡ ምንም ፡ አጣሁ
ግን ፡ መድሃኒቴን ፡ ስጠራው
ሲበራ ፡ አየሁ ፡ የድል ፡ ጮራው

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ኃይል ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ጉልበት ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ፈውስ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

አልናድ ፡ ያለው ፡ ተራራ
ተናደ ፡ የሱን ፡ ሰም ፡ ስጠራ
አልሞላ ፡ ያለ ፡ ሸለቆ
ታየኝ ፡ በጌታዬ ፡ ሞልቶ
በታምራቱ ፡ አስደነቀኝ
የስሙን ፡ ኃይል ፡ አሳየኝ

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ኃይል ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ጉልበት ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ፈውስ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

ሞቴን ፡ በሞቱ ፡ የሻረው
ስሞ ፡ መድሃኒቴ ፡ የሆነው
እስከ ፡ ዛሬም ፡ አልተረታ
ዘላለም ፡ የማይረታ
ለእርሱ ፡ ልዘምር ፡ በደስታ
ይክበር ፡ እያልኩ ፡ በዕልልታ

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ኃይል ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ጉልበት ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ፈውስ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

እያሪኮ ፡ ቢሆን ፡ ጐልያድ
በፊታችሁ ፡ ቢገደገድ
የኢየሱስን ፡ ሥም ፡ ስንጠራ
ይወድቃሉ ፡ በየተራ
ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ሥም ፡ ያለው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ታላቅ ፡ ነው

አዝ፦ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ኃይል ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ጉልበት ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ፈውስ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue