Maserow Siseber (ማሰሮው ፡ ሲሰበር)

ማሰሮው ፡ ሲሰበር ፡ ድብቁ ፡ ብርሃን ፡ ይወጣል
ስንዴው ፡ ሲበሰብስ ፡ ቡቃያው ፡ ብዙ ፡ ያፈራል
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የተሰበረ ፡ ልብ ፡ ያሻኛል

ድምፅህን ፡ እንድሰማ ፡ የተግሳጽ ፡ ይሁን ፡ ወይም ፡ የምክር
በድንግዝግዝ ፡ ጊዜ ፡ ወድቄ ፡ እንዳልሰበር
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የተከፈተ ፡ ጆሮ ፡ ያሻኛል

አንተን ፡ ለመመልከት ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊቴ ፡ ስትሄድ
ወደ ፡ ቀጠሮአችን ፡ ቦታ ፡ በብርሃንህ ፡ እንድራመድ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ጤንነት ፡ ያለው ፡ ዓይን ፡ ያሻኛል

ሰላምን ፡ ለማውራት ፡ የምሥራች ፡ ይዤ ፡ እንድሮጥ
ፅድቅን ፡ ለተጠሙ ፡ ምንጩን ፡ እነሆ ፡ ለማለት
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የሚራመዱ ፡ እግሮች ፡ ያሹኛል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue