አይወስንህ ፡ ሁኔታ

አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ
አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x)

ከሠማይ ፡ በታች ፡ ፍጥረት ፡ የሚያገኘው
ደስታው ፡ የማይጸና ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ታዲያ ፡ ምብዛቱ ፡ ጥቅሙ ፡ ምንድን ፡ ነው
ምኞቱ ፡ መሻቱ ፡ ንፋስ ፡ መከተሉ

አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ
አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x)

የዚች ፡ ዓለም ፡ ውብት ፡ መቼ ፡ ደስታ ፡ ይሰጣል
ትናንት ፡ የነበረ ፡ ድንገት ፡ ከእጅ ፡ ያመልጣል
ቋሚ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
የሚጸና ፡ ደስታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ
አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x)

መብዛትን ፡ መጉደልን ፡ ሁሉ ፡ ተምሬያለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
ነገር ፡ ተለዋዋጭ ፡ መሆኑን ፡ አየሁኝ
የሚጸና ፡ ደስታ ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ

ደስታዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ
ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ብቻ
እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ብቻ
ሃብቴ ፡ አንተ ፡ ብቻ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ
በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ
አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue