አዝ፦
ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ
የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ
ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ
የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ
ሰዓቱ ፡ ሊሞላ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው
መለከት ፡ ሊነፋ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው
ነገሩ ፡ ሊያከትም ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው
ጌታም ፡ ከተፍ ፡ ሊል ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው
አዝ፦ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ
የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ
ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ
የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ
ሰማያት ፡ ሲከብዱ ፡ ደመናው ፡ ሲጠቁር
ምድራችን ፡ ስታምር ፡ ነገር ፡ ሲቀያየር
ምን ፡ አዚም ፡ ኖረብን ፡ እንዳናይ ፡ ጊዜ ፡ አጥሮን
ተው ፡ ነቃ ፡ እንበል ፡ እናቁም ፡ አንቅልፍን
አዝ፦ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ : ገሰገሰ
የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ
ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ
የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ
ሰው ፡ ሲተራመስ ፡ ሞትን ፡ ለመሳለም
ከአምላክ ፡ ተለይቶ ፡ ለኃጢያት ፡ ሲታመን
ጠቢቡ ፡ እንኳን ፡ ሲስት ፡ በሰይጣን ፡ ሲታለለ
ተነሱ ፡ አንናገር ፡ ለነፍስ ፡ እንታገል
አዝ፦ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ
የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ
ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ
የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ
እርሱ ፡ ያልሞተ ፡ እራሱን ፡ ያልከዳ
ጌታ ፡ የማይገዛው ፡ ለኃጥያት ፡ ያልታገለ
በምኑ ፡ ይመስክር ፡ ልቡ ፡ ይንቀጠቀጣል
ዋጋም ፡ ክፈል ፡ ሲባል ፡ ትቶ ፡ ይፈረጥጣል
አዝ፦ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ
የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ
ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ
የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ