Wude yene new (ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው)

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

አልተሳሳትኩም ፡ እኔ ፡ በምርጫዬ
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻላል ፡ ብዬ
ነፍሴን ፡ ሊታደግ ፡ በሩን ፡ ላንኳኳው
ከፈትኩለት ፡ ልቤን ፡ ኢየሱሴን ፡ ላስገባው
እርሱም ፡ አሜን ፡ ሕይወቴን ፡ ወረሰው

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

ሞልቶልኝ ፡ ከማጣ ፡ ኢየሱሴን
አልፈልግም ፡ መርጣለሁ ፡ ሞቴን
ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ወዴት ፡ ሄዳለሁ
ልለየው ፡ አልችልም ፡ እጅግ ፡ ወደዋለሁ
ከእርሱ ፡ የተነሳ ፡ ከሞት ፡ ድኛለሁ

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

አይለወጥም ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም
አምነዋለው ፡ ኢየሱስ ፡ አይከዳኝም
በዘለዓለም ፡ ፍቅሩ ፡ ስቦኛል ፡ ወዶኛል
እስከ ፡ ሽበት ፡ ቢሆን ፡ እርሱ ፡ ይሸከመኛል
ሰልችቶ ፡ ውዴ ፡ መቼ ፡ ይጥለኛል

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

ውርደቴን ፡ በክብር ፡ ለውጦልኝ
የማዳንን ፡ ልብስ ፡ አለበሰኝ
የባርነቴም ፡ ቀንበር ፡ ሰብሮልኝ
ቀና ፡ ብዬ ፡ እንድሄድ ፡ ኢየሱስ ፡ አደረገኝ
እሰይ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይንገስልኝ

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

ከምንም ፡ በላይ ፡ አዎ ፡ የሚበልጠው
ታማኙ ፡ ኢየሱስ ፡ ባልንፈራዬ ፡ ነው
ቃሉ ፡ ይጣፍጣል ፡ ልብን ፡ ይደርሳል
ውዴ ፡ እኮ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ማንስ ፡ ይመስለዋል
ምርጫዬ ፡ ነው ፡ እርሱም ፡ እኔን ፡ መርጧል

አዝ፦ ውዴ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ የእርሱ ፡ ነኝ (፪x)
ከሌላው ፡ ወዳጄ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ የሚበልጥብኝ
ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ
በእርሱ ፡ አትምጡብኝ ፡ ኢየሱሴን ፡ አትንኩብኝ

እኔ ፡ ወደዋለሁ ፡ ምኞቱን ፡ አውቃለሁ
አላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው
አላማውም ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue