የሚያስፈልገኝን ፡ ያውቃል (Yemiyasfelegegnen Yawqal)

የሚያስፈልገኝን ፡ እርሱ ፡ ያውቃል
የሰማይ ፡ አባቴ ፡ ለኔ ፡ ያስባል
እጆቼን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ዘረጋለሁ
በዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እታመናለሁ

የሚያስጨንቀን ፡ በእርሱ ፡ ጥዬ
እታመናለሁኝ ፡ በጌታዬ
ጽድቁና ፡ መንግሥቱን ፡ እሻለሁኝ
ክብሩን ፡ እያየሁኝ ፡ እጠግባለሁኝ

ላመልከው ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የፈጠረኝ
ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ላይገዛኝ
እያሞጋገስኩኝ ፡ ታላቅ ፡ ስሙን
አመልከዋለሁኝ ፡ እግዚአብሔርን

የጠራኝ ፡ የለየኝ ፡ የቀደሰኝ
ለእርሱ ፡ ካህን ፡ ልሆን ፡ ነው ፡ የቀባኝ
እርሱ ፡ ያደረገኝ ፡ እሆናለሁ
የኣምላኬን ፡ በጐነት ፡ አወራለሁ

መልካሙን ፡ ስራውን ፡ የጀመረው
የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው
እስከ ፡ ክርስቶስ ፡ ቀን ፡ ሊፈጽመው
ይችላል ፡ አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው

Recently Listened by

1 comments

:: / ::
::
/ ::

Queue