Bedenq Aterareh (በድንቅ ፡ አጠራርህ)

አዝ፦ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ
በእረፍት ፡ ውሃ ፡ ዘንድ ፡ የመራኸኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳደርከኝ
በአለት ፡ ንቃቃት ፡ የሰወርከኝ
ተግተህ ፡ የጠበከኝ ፡ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ

በግብጻውያን ፡ በደል ፡ በዓመጻቸው
ቁጣህ ፡ ከላይ ፡ ወርዶ ፡ ሲፈጃቸው
ደምህ ፡ ተቀብቶ ፡ በመቃኔ
ምክንያት ፡ ሆኖልኛል ፡ ለመዳኔ
ተጠነቀክልኝ ፡ እንዳልጠፋ
ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይንሰራፋ

አዝ፦ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ
በእረፍት ፡ ውሃ ፡ ዘንድ ፡ የመራኸኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳደርከኝ
በአለት ፡ ንቃቃት ፡ የሰወርከኝ
ተግተህ ፡ የጠበከኝ ፡ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ

በኮሬብ ፡ ተራራ ፡ በእሳት ፡ አምሳል
ለነብዩ ፡ ሙሴ ፡ ተገልፀሃል
በእኔም ፡ ልብ ፡ አንድደህ ፡ የፍቅር ፡ እሳት
ምስኪኑን ፡ ሕይወቴን ፡ ስታጋያት
አይቻለሁ ፡ እና ፡ እንዳቅሜ
አመሰግናለው ፡ ይኸው ፡ ቆሜ

አዝ፦ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ
በእረፍት ፡ ውሃ ፡ ዘንድ ፡ የመራኸኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳደርከኝ
በአለት ፡ ንቃቃት ፡ የሰወርከኝ
ተግተህ ፡ የጠበከኝ ፡ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ

ከኃጤአቴ ፡ በቀር ፡ ከመርከሴ
የማውቀው ፡ የለኝም ፡ ስለራሴ
አንተን ፡ ግን ፡ አውቃለሁ ፡ ስታድንኝ
የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ ስትሆነኝ
በፍቅር ፡ ይዘኸኛል ፡ በውዴታ
እኔም ፡ ላመስግንህ ፡ በእልልታ (፪x)

አዝ፦ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ
በእረፍት ፡ ውሃ ፡ ዘንድ ፡ የመራኸኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳደርከኝ
በአለት ፡ ንቃቃት ፡ የሰወርከኝ
ተግተህ ፡ የጠበከኝ ፡ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ

አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ያገናኘን
እንደ ፡ አባት ፡ እና ፡ ልጅ ፡ ያቆራኘን
ለእኔ ፡ ያሰብከው ፡ ያኔ ፡ ድሮ
ዛሬ ፡ ተፈፀመ ፡ ዘመን ፡ ቆጥሮ
ያረካህ ፡ እንደሆን ፡ ይኸው ፡ መልሴ
ምስጋና ፡ እና ፡ ክብር ፡ ከውዳሴ

አዝ፦ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ
በእረፍት ፡ ውሃ ፡ ዘንድ ፡ የመራኸኝ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳደርከኝ
በአለት ፡ ንቃቃት ፡ የሰወርከኝ
ተግተህ ፡ የጠበከኝ ፡ እንዳልጠፋ
መድሃኒዓለም ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue