Egziabher Maninim Tilo Ayawkimina (እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅም)

ብዙ ፡ ተዓምራቶችን ፡ ሲሰራ ፡ ያያችሁ
ሁልጊዜ ፡ በቃሉ ፡ እንዲህ ፡ ሲናገራችሁ
ማነው ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ/ጌታ ፡ የሚሆንላችሁ
በመከራው ፡ ጌዜ ፡ ከእርሱ ፡ የሸሻችሁ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና
ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና
የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና
አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና

ቅዱሳኖች ፡ ጽኑ ፡ ጨለማው ፡ ይነጋል
ኢየሱስ ፡ ሲያስበን ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል
ፀሐይ ፡ ሲወጣበት ፡ ተኖ ፡ እንደሚጠፋ
ቀናችን ፡ ይሄዳል ፡ ያስቆረጠን ፡ ተስፋ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና
ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና
የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና
አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና

እግዚአብሔር ፡ ከልቡ ፡ አያስጨንቀንም
ሕዝቡን ፡ ለተኩላዎች ፡ አሳልፎ ፡ አይሰጥም
ቢያሳዝነን ፡ እንኳን ፡ ልቡ ፡ ሚራራ ፡ ነው
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ መስማማት ፡ ያ ፡ ነው ፡ የሚሻለው (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና
ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና
የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና
አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና

ክለቅሶ ፡ ከሃዘን ፡ ከማማረር ፡ ሕይወት
ክውድቀት ፡ ከድካም ፡ ፈጥኖ ፡ ሚያነሳበት
የጠፉትን ፡ ሁሉ ፡ የሚፈልግበት
እግዚአብሔር ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ የሚጐብኝበት (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና
ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና
የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና
አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና (፪x)

For nylig lyttet af

0 kommentarer
    Ingen kommentarer fundet

:: / ::
::
/ ::