Melaekt Adis Qenie (መላዕክት ፡ አዲስ ፡ ቅኔ).mp3

በዙፋኑ ፡ ላይም ፡ በተቀመጠው ፡
በቀኝ ፡ እጁ ፡ ላይ ፡ በውስጥና ፡ በኋላ ፡ የተጻፈበት
በሰባትም ፡ ማኅተም ፡ የተዘጋ ፡ መጽሃፍ ፡ አየሁ ።
ብርቱም ፡ መልአክ ፡ "መጽሃፉን ፡ ይዘረጋ ፡ ዘንድ ፤
ማኅተሞቹንም ፡ ይፈታ ፡ ዘንድ ፡ የሚገባው ፡ ማነው?" ፡
ብሎ ፡ በታላቅ ፡ ድምጽ ፡ ሲያውጅ ፡ አየሁ ።
በሰማይም ፡ ቢሆን ፤ በምድርም ፡ ቢሆን ፤
ከምድርም ፡ በታች ፡ ቢሆን ፤ መጽሃፉን ፡ ሊዘረጋ ፡ ወይም ፡
ሊመለከተው ፡ ማንም ፡ አልተቻለውም ። መጽሃፉንም ፡ ሊዘረጋ ፡
ወይም ፡ ሊመለከተው ፡ የሚገባው ፡ ማንም ፡ ስላልነበረ ፡
እጅግ ፡ አለቀስኩ ። ከሽማግሌዎቹም ፡ አንዱ
"አታልቅስ ፡ እነሆ ፡ ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ ፡
እርሱም ፡ የዳዊት ፡ ስር ፡ መጽሃፉን ፡ ይዘረጋ ፡ ዘንድ ፡
ሰባቱንም ፡ ማኅተም ፡ ይፈታ ፡ ዘንድ ፡ ድል ፡ ነስቷል" ፡ አለኝ ። [1]

መልአክት ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ይዘምራሉ
እንዲህ ፡ እያሉ ፡ መጽሃፍት ፡ ወስደን
ማኅተሞቹን ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል
ይገባሃል (፫x) ፡ ታርደሃልና ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል

ሌሎች ፡ ሲሉ ፡ ሰማሁ ፡ የታረደው ፡ በግ
ሃይልና ፡ ባለጠግነት ፣ ጥበብ ፡ ብርታት ፣ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ በረከት
ይቀበል ዘንድ ፡ ይገባዋል (፪x) ፡ በረከትን ፡ ይቀበል ፡ ዘንድ ፡ ይገባዋል

በረከት ፡ እና ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ሃይልም
ከዘለዓለም ፡ እስከዘለዓለም ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው ፡ በጉ ፡ ይሁን
ደግሞ ፡ እያሉት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ለበጉ ፡ ክብር
ይቀኛሉ ፡ ይዘምራሉ ፡ ያዜማሉ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue