Endiet Lefra (እንዴት ፡ ልፍራ)

  • 16
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Endiet Lefra (እንዴት ፡ ልፍራ)

Lyrics

እንዴት ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር
እግዚአብሔር ፡ ሆኖልኝ ፡ ሞገስ (፪x)

አምላካችን ፡ መጠጊያችንና ፡ ኃይላችን ፡ ነህ
ባገኘን ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን ፡ አሃሃ ፡ ረዳታችን
ስለዚህ ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ
ተራሮች ፡ ወደባሕር ፡ ልብ ፡ ቢወሰዱ
እኔ ፡ አልፈራም ፡ አሃሃ ፡ እኔ ፡ አልፈራም

ማለፍ ፡ የማይቻለውን ፡ በአንተ ፡ አለፍኩ
አስፈሪውን ፡ ጨለማ ፡ ተሻገርኩኝ (፫x)
ሁሉን ፡ በአንተ ፡ አለፍኩኝ
ክብርህን ፡ ይኸው ፡ አየሁ ፡ ጨለማው ፡ ሰገፈፍ
አዲስ ፡ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ ክበር ፡ ያከበርከኝ

አምላካችን ፡ መጠጊያችንና ፡ ኃይላችን ፡ ነህ
ባገኘን ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን ፡ አሃሃ ፡ ረዳታችን
ስለዚህ ፡ ምድር ፡ ብትናወጥ
ተራሮች ፡ ወደባሕር ፡ ልብ ፡ ቢወሰዱ
እኔ ፡ አልፈራም ፡ አሃሃ ፡ እኔ ፡ አልፈራም

ለህዝቡ ፡ የሚያዝን ፡ ፍፁም ፡ የሚራራ
አማኑኤል ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ ከኛ ፡ ጋራ (፫x)
ስናዝን ፡ አፅናንቶን ፡ ኃይልም ፡ ጉልበት ፡ ሰጥቶን
መከራችንን ፡ ረሳን ፡ አምላካችን ፡ በእኛ ፡ ከብሮ

:
/ :

Queue

Clear