• 280
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Dagmawi Tilahun--Geta Ale Kegone-Amesegnalehu (አመሰግናለሁ)

አዝ፦ የልቤ ፡ ደረሰ ፡ ያሰብኩት ፡ ተሳካ
አደራ ፡ የሰጠሁት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x)

ዛሬማ ፡ አርፌ ፡ ተደላድያለሁ
ሥራዬ ፡ ተሰርቶ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

በሬን ፡ ዘግቼ ፡ የለመንኩት
ምነው ፡ ባረገው ፡ ጌታን ፡ ያልኩት
በእጥፍ ፡ ላከው ፡ ቀዶ ፡ ከሰማይ
የልቤ ፡ ደርሷል ፡ ካሰብኩት ፡ በላይ (፪x)

አዝ፦ የልቤ ፡ ደረሰ ፡ ያሰብኩት ፡ ተሳካ
አደራ ፡ የሰጠሁት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x)

ዛሬማ ፡ አርፌ ፡ ተደላድያለሁ
ሥራዬ ፡ ተሰርቶ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

የጌታን ፡ ውለታ ፡ በጥዋት ፡ በማታ
መች ፡ እዘነጋለሁ ፡ እዘምረዋለሁ
የጌታን ፡ ውለታ ፡ በጥዋት ፡ በማታ
መች ፡ እዘነጋለሁ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ የልቤ ፡ ደረሰ ፡ ያሰብኩት ፡ ተሳካ
አደራ ፡ የሰጠሁት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x)

ዛሬማ ፡ አርፌ ፡ ተደላድያለሁ
ሥራዬ ፡ ተሰርቶ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

(የልቤ ፡ ደረሰ) (፫x)

አላየሁኝም ፡ ፃድቅ ፡ ሲጣል
ዘሩም ፡ ሲለምን ፡ አጥቶ ፡ እህል
ጌታ ፡ ታሪኬን ፡ እንዲህ ፡ አርጐታል
የልቤን ፡ ሃሳብ ፡ አሳክቶታል (፪x)

የጌታን ፡ ውለታ ፡ በጥዋት ፡ በማታ
መች ፡ እዘነጋለሁ ፡ እዘምረዋለሁ
የጌታን ፡ ውለታ ፡ በጥዋት ፡ በማታ
መች ፡ እዘነጋለሁ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

:: / ::
::
/ ::

কিউ