amharic gospel mezmur

ገመዴ ፡ ባማረ ፡ ውብ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ (፪x)
እርስቴም ፡ በእርሱ ፡ በኢየሱሴ ፡ ተዋበችልኝ (፪x)
እፎይ ፡ አሰኘኝ ፡ ጌታ ፡ ቤቴ ፡ ገብት
መራራ ፡ የሆነውን ፡ ታሪኬን ፡ ለውጦ (፪x)

አዝ፦ መጐብኛዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ
ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ በዚህ ፡ ጌታ
አርፌያለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ
ሲደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ
ጌታ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፬x)

በምድረበዳ ፡ ውስጥ ፡ ከአለት ፡ ውኃ ፡ አፍልቆ
እኔን ፡ አረካልኝ ፡ መገፋቴን ፡ አይቶ
የዘመናት ፡ ለቅሶ ፡ እምባ ፡ ታበሰልኝ
ልዑል ፡ ከዙፋኑ ፡ ለእኔ ፡ ሲነሳልኝ
ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ አሄ
ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
አምልኮ ፡ አሄ ፡ አምልኮ ፡ አሄ ፡ አሄ
አምልኮ ፡ አሄ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፬x)

አዝ፦ መጐብኛዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ
ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ በዚህ ፡ ጌታ
አርፌያለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ
ሲደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ
ጌታ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፬x)

መጐብኛዬ ፡ ጊዜው ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል
የሃዘኑ ፡ ጊዜ ፡ አልፎ ፡ ደስታ ፡ ቤቴ ፡ ሞልቷል
ጠላት ፡ ዐይኑ ፡ እያየ ፡ ይሄው ፡ ጉብኝቴ
አከናወነልኝ ፡ ሁሉንም ፡ አባቴ
ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ምሥጋና ፡ አሄ ፡ አሄ
ምሥጋና ፡ አሄ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ዝማሬ ፡ አሄ ፡ ዝማሬ ፡ አሄ ፡ አሄ
ዝማሬ ፡ አሄ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፮x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue