Eyesusin Lebseh (ኢየሱስን ፡ ለብሰህ)

የሚቀጠቅጥ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ወጥቷል ፡ በጠላት ፡ ተከበሃል
ክርስቲያን ፡ ተጠንቀቅ ፡ ዙሪያህን ፡ አስተውል
ጉልበትህ ፡ አይላላ ፡ ጠንክረህ ፡ ተዋጋ
ብድራትን ፡ አይተህ ፡ ያለልህን ፡ ዋጋ

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ
የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ
በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ

በጦርነት ፡ ላይ ፡ መቁሰልም ፡ አለ ፡ ሞትም ፡ ቢሆን ፡ ጥቅም ፡ ነው
ለጨለማው ፡ ገዢ ፡ እጅህን ፡ አትስጠው
እስከ ፡ ሞት ፡ ታመን ፡ ነፍስህን ፡ አታክብራት
ለታመነው ፡ ፈጣሪ ፡ አሳልፈህ ፡ ስጣት

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ
የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ
በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ

ባለጋራህ ፡ ዲያብሎስ ፡ ሊውጥህ ፡ እያገሳብህ ፡ ነውና
ከድምፁ ፡ አትፍራ ፡ አባትህ ፡ አለና
መንጋጋውን ፡ ዘግቶ ፡ ከአፉ ፡ ያስጥልሃል
ከቶም ፡ እንደማይጥልህ ፡ በግልጽ ፡ ያሳየዋል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ
የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ
በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ

የውጊያው ፡ ጊዜ ፡ አሁን ፡ ነው ፡ ወንድም
ተነስ ፡ ተጋጠመው ፡ ድል ፡ ትነሳዋለህ
በርትተህ ፡ ታገለው ፡ የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ጋሻ ፡ ይሆንሃል
ለአገርህም ፡ አብቅቶ ፡ አክሊል ፡ ይሰጥሃል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ ለብሰህ
የጦር ፡ ዕቃህን ፡ አንስተህ
በእርሱ ፡ መልካም ፡ ጦርነት ፡ ተዋጋ
ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል ፡ ለድሉ ፡ አትስጋ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue