የማልወጣው ፡ ይመስለኝና
እምነቴ ፡ ፍፁም ፡ ይከዳኝና
ደንግጬ ፡ ሳለሁ ፡ በሥጋት ፡ ስፈርስ
አይዞህ ፡ ይለኛል ፡ ኢየሱስ
አዝ፦ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ለመድኃኒዓለም (፬x)
የታል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብዬ ፡ ስናገር
ማየት ፡ ሲሳነኝ ፡ ዓይኔ ፡ ሲታወር
ብርሃን ፡ ሆኖ ፡ ሁሉን ፡ ሊያሳየኝ
ኢየሱስ ፡ ብቅ ፡ ሲል ፡ ይኸው ፡ ታየኝ
አዝ፦ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ያለፈው ፡ ውለታ ፡ ትጋቱ ፡ ሁሉ
ቢዘነጋልኝ ፡ ያ ፡ ብርታት ፡ ኃይሉ
መፍገምገም ፡ ይዞት ፡ ጠላቴ ፡ ሲያዝ
ኢየሱስ ፡ ብቅ ፡ አለ ፡ እኔን ፡ ሊያግዝ
አዝ፦ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ፍቅሩ ፡ የሚጣፍጥ ፡ ልዩ ፡ ነውና
ትዕግሥቱም ፡ ፍፁም ፡ አያልቅምና
አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና
ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
አዝ፦ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ለመድኃኒዓለም (፬x)