ወንድሜ ፡ ንቃ (Wendemie Neqa)

አዝ፦ ወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ጌታ ፡ እንደ ፡ ሌባ ፡ ይመጣልና
ቀን ፡ . (1) . ፡ አታውቅምና
ስለዚህ ፡ ንቃ ፡ መብራትህ ፡ ይብራ
በፍጻሜው ፡ ቀን ፡ እንዳትፈራ

አዝ፦ ወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ስሙን ፡ በመፍራት ፡ ለሚኖሩት
የጽቅድ ፡ ጸሃይ ፡ ይወጣል ፡ በእውነት
እምላክህን ፡ ፍራ ፡ ጠብቀው ፡ ተግተህ
በክብር ፡ ሲገለጥ ፡ እንዳያፍርብህ

አዝ፦ ወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ከማያምኑ ፡ ጋር ፡ ህብረት ፡ አይኑርህ
በማይመችህ ፡ መንገድ ፡ አትሂድ
ይልቅ ፡ ዘመኑን ፡ መርምር ፡ አጥብቀህ
በከንቱ ፡ አንዳያልፍ ፡ ጐልማሳነትህ

አዝ፦ ወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ሰዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

እርሱን ፡ ከሚሉ ፡ ጋር ፡ ደስ ፡ ይበልህ
ከሰው ፡ ሁሉ ፡ ጋር ፡ ሰላም ፡ ይኑርህ
እጅጉን ፡ ንቃ ፡ ጊዜው ፡ ተቃርቧል
አሜን ፡ ይሆናል ፡ በርግጥ ፡ ይመጣል

አዝ፦ ወንድሜ ፡ ንቃ ፡ አትተኛ (፪x)
ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ (፪x)

ጌታ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ቀርቧል ፡ ስዓቱ ፡ የመገለጡ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue