Libarkew Getayen Libarkew (ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው)

(ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው) (፬x)
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ ባረከኝ ፡
የረገጥኩትን ፡ አወረሰኝ
ታዲያ ፡ ምን ፡ ይሰጣል ፡ለጌታ
እስኪ ፡ ከፍ ፡ አርጉልኝ ፡ በልልታ

የነገረኝን ፡ በሙሉ ፡ እስከሚያደርግልኝ ፡ ታምኖ
ለክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ በሃሩር ፡ ጥላዬ ፡ ሆኖ
ሲጠማኝ ፡ ምንጭ ፡ አፈለቀ ፡ ሲርበኝ ፡ ደግሞ ፡ አጐረሰኝ
ሰው ፡ ዓይንህ ፡ ለአፈር ፡ ሲለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አንዴም ፡ ሳይሸሸኝ
እንደበደሌ ፡ አልከፈለኝ ፡ ምህረቱ ፡ ስለእኔ ፡ በዝቷል
በነፍስና ፡ በሥጋዬ ፡ በረከቱ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቷል ፡
እንዴት ፡ ታዲያ ፡ ዝም ፡ ልበል ፡ ይህንን ፡ ሁሉ ፡ አይቼ
ልስገድ ፡ ልውደቅ ፡ በግንባሬ ፡ ማደሪያው ፡ ቤቱ : ገብቼ

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን

በደሌ ፡ በፊቱ ፡ በዝቶ ፡ ያለቀ ፡ የሞትኩ ፡ ሲመስለኝ
የጠላቴ ፡ማስፈራራት ፡ ጩኸቱ ፡ ሲያርበደብደኝ
በዘመርኩበት ፡ አንደበት ፡ ሙሾ ፡ ለመውረድ ፡ ስዳዳ
የሞትን ፡ ወሬ ፡ ሰምቼ ፡ ለነፍሴ ፡ ሞትን ፡ ላረዳ
ስዋከብ ፡ ከዚህ ፡ ወደዚያ ፡ ጭንቀቴን ፡ አይቶ ፡ ደረሰ
የተዋጋኝን ፡ ተዋጋው ፡ እቅዱን ፡ አፈራረሰ
ዛሬማ ፡ በኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ምሥጋና ፡ እዘምራለሁ
ሰው ፡ ያደረገኝን ፡ አምላኬን፡ በዜማ ፡ ፡ እባርካለሁ

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን

በሰማያዊ ፡ በረከት ፡ በመንፈስ ፡ ባርኮ ፡ ባረከኝ
የምድሩን ፡ አላጣሁም ፡ ይልቁን ፡ አትረፈረፈኝ
ሳይሰለች ፡ የተሸከመኝ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ ቤቴን ፡ ባረከው
ዓለም ፡ የነፈገችኝን ፡ ኢየሱስ ፡ እጥፍ ፡ አረገው
የሱስን ፡ ብሎ ፡ ወዝ ፡ አጣ ፡ ያሉ ፡ዛሬ ፡ ይሄው ፡ አፈሩ
ጌታ ፡ ሞገሴ ፡ መሆኑን ፡ በአፋቸው ፡ መሰከሩ
ወጥመድ ፡ ቢዘጋጅልኝም ፡ ኢየሱስ ፡ እየቀደመ
ሕይወቴን ፡ በረከት ፡ ሞላው፡ ደረቅ ፡ በትር ፡ ለመለመ

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬን

እናንተም ፡ አንደኔው ፡ ጌታ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ የባረካችሁ
በተሰደዳችሁበት ፡ ምድር ፡ እጅግ ፡ ያበዛችሁ
የገዛችሁን ፡ ኢየሱስ ፡ ከእግራችሁ ፡ ላስገዛላችሁ
ጅራት ፡ ሳይሆን ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ የሁሉ ፡ እራስ ፡ ያረጋችሁ
እስኪ ፡ እናንተው ፡ ንገሩኝ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምን ፡ ይከፈላል
ወደር ፡ ለሌለው ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ ምላሻ ፡ ምንስ ፡ ይሰጣል
ከአድማስ ፡ አድማስ ፡ ባሻገር ፡ ሙገሳ ፡ ክብር ፡ ሙገሳ ፡ ይድረሰው
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ በአንደበቱ ፡ ይቀድሰው

አዝ
ልባርከው ፡ ጌታዬ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue