Maerege Neh (ማዕረጌ ፡ ነህ)

አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል
ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል
ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ
ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ

ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

ያማረብኝ ፡ በአንተ ፡ አሃሃሃ
ወግ ፡ ያየሁት ፡ በአንተ ፡ አሃሃሃ
ሚስጥሩ ፡ ያልገባው ፡ ጥግ ፡ ሆኖ ፡ ቢተቸኝ
ያሰኘውን ፡ ይበል ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ አይረብሸኝ
ከርግሮህ ፡ ስር ፡ ወድቂ ፡ አሃሃሃ
ፈቅጄ ፡ አመልካለሁ ፡ አሃሃሃ
መሸ ፡ ነጋ ፡ አልልም ፡ ኑሮዬ ፡ አምልኮ ፡ ነው

አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል
ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል
ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ
ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ

ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

ያ ፡ ውድ ፡ መዓዛው ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
የከበረውን ፡ ሽቶ ፡ ከእግርህ ፡ ስር ፡ ልስበረው
ክብሬን ፡ እየጣልኩ ፡ ክብር ፡ እሰጥሃለሁ
በሁለንተናዬ ፡ ላመልክህ ፡ ቆርጫለሁ

አመልካለሁ ፡ ክብሬን ፡ እየጣለኩ
አመልካለሁ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃለሁ
አመልካለሁ ፡ የመኖሬ ፡ ትርጉም
አመልካለሁ ፡ ሚስጥሩ ፡ በአንተ ፡ ነው (፪x)

ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

አዝ:- ማን ፡ እንዳንተ ፡ ይሆናል
ማንስ ፡ ልብን ፡ ይረዳል
ለእኔስ ፡ ሁሉን ፡ ሆንክልኝ
ጌታ ፡ በአንተ ፡ አማረብኝ

ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
ትምክቴ/ውበቴ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue