አዝ፦ ምስኪኑ ፡ ተነሳ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ አሃሃሃሃ
ሊያከብርህም ፡ ቆመ ፡ በአደባባይ ፡ አሃሃሃሃ
በንጉሥ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ኦሆሆሆሆ
ይሰዋል ፡ ምሥጋናን ፡ አብዝቶ ፡ ኦሆሆሆሆ (፪x)
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ገልብጦለት
ሞቱን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ ቀይሮለት
ፍጥረት ፡ እየሰማ ፡ ይዘምራል
እግዚአብሔርን ፡ ወዶ ፡ ያመልከዋል (፪x)
አዝ፦ ምስኪኑ ፡ ተነሳ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ አሃሃሃሃ
ሊያከብርህም ፡ ቆመ ፡ በአደባባይ ፡ አሃሃሃሃ
በንጉሥ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ኦሆሆሆሆ
ይሰዋል ፡ ምሥጋናን ፡ አብዝቶ ፡ ኦሆሆሆሆ (፪x)
ጠላቱ ፡ ሊያጠፋው ፡ ሲዝትበት
መለከት ፡ በዙሪያው ፡ ሲያስነፋበት
እግዚአብሔር ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ አለ
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ገለበጠ (፪x)
አዝ፦ ምስኪኑ ፡ ተነሳ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ አሃሃሃሃ
ሊያከብርህም ፡ ቆመ ፡ በአደባባይ ፡ አሃሃሃሃ
በንጉሥ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ኦሆሆሆሆ
ይሰዋል ፡ ምሥጋናን ፡ አብዝቶ ፡ ኦሆሆሆሆ (፪x)
የልመናው ፡ ቃል ፡ ሰምቶለታል
ጌታ ፡ በአደባባይ ፡ አቁሞታል
ጠላቱ ፡ እያየ ፡ እየሰማ
ይዘምራል ፡ በአዳዲስ ፡ ዜማ (፪x)
አዝ፦ ምስኪኑ ፡ ተነሳ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ አሃሃሃሃ
ሊያከብርህም ፡ ቆመ ፡ በአደባባይ ፡ አሃሃሃሃ
በንጉሥ ፡ ፈረስ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ኦሆሆሆሆ
ይሰዋል ፡ ምሥጋናን ፡ አብዝቶ ፡ ኦሆሆሆሆ (፪x)
ጌታ ፡ ደም ፡ ግባቱ ፡ ሆኖለታል
በሞገስ ፡ ላይ ፡ ሞገስ ፡ አልብሶታል
እርሱም ፡ ያመልከዋል ፡ በመገረም
እያለ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር/ጌታ ፡ ያል ፡ የለም (፪x)
. (1) . ፡ እንደ ፡ ጌታ (፮x)
እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይሆናል (፫x) ፡ እንደጌታ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይሆናል (፫x) ፡ እንደጌታ
(1) . ፡ እንደ ፡ ጌታ (፮x)
እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይሆናል (፫x) ፡ እንደጌታ
እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ ይሆናል (፫x) ፡ እንደጌታ
If you appreciate the work we do at Wongelnet and would like to support our ongoing development, research, and the efforts of our support staff, we’d be incredibly grateful if you could buy us a coffee.
Your support not only helps us keep the lights on but also fuels our passion to continue improving the platform and providing you with the best possible service. Every little bit helps us stay focused on delivering the features and updates that matter most to you.