Abetu Mebarekin Barken (አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን)

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ያቤጽንም ፡ ሰምተሃል ፡ እንደዚህ ፡ ሲለምንህ
ነፍሱን ፡ ባርከህለታል ፡ አገሩንም ፡ አስፍተህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

በልጅህ ፡ ስቃይና ፡ በጣር ፡ የተወለድን
እኛም ፡ ፍሬዎችህ ፡ ነን ፡ አስባስበህ ፡ ጠብቀን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ከፊትህ ፡ አትጣለን ፡ እንማጸንሃለን
በሞገስህ ፡ አስበን ፡ በምህረትህ ፡ ጐብኘን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ሰማያቱም ፡ ይከፈቱ ፡ መንፈስህ ፡ ይፍሰስልን
ሕይወታችን ፡ ትረስርስ ፡ ነፍሳችን ፡ ትጥገብልን

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ብቻችንን ፡ አንቅር ፡ አብዛን ፡ እየባረክህ
አበልጽገን ፡ በፀጋህ ፡ ታደገን ፡ በቃልህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

እግዚአብሔርን ፡ በማወቅ ፡ ምድር ፡ እስክትሞላ
ምልጃችን ፡ ይቀጥላል ፡ ጉልበታችን ፡ ሳይላላ

አዝ፦ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
አገራችንን ፡ አስፋ
እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን
አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue