Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ይኖራል (፪x)
ከትከሻው ፡ መሃል ፡ ተማምኖ ፡ ያድራል (፪x)

ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ)
ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ)
እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ)

አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ
የፀና ፡ ግንብ ፡ ነውና ፡ በሥሙ ፡ እጓደዳለሁ
ገና ፡ ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ ከማያልቀው ፡ ቸርነቱ
በዘይት ፡ ሊያለመልመኝ ፡ ተክሎኛል ፡ እና ፡ በቤቱ

እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ
በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፪x)

አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ይኖራል (፪x)
ከትከሻው ፡ መሃል ፡ ተማምኖ ፡ ያድራል (፪x)

ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ)
ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ)
እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ)

የሕይወትን ፡ ምንጭ ፡ አግኝቼ ፡ ከተድላው ፡ ፈሳሽ ፡ ጠጥቼ
ዳግመኛ ፡ እኔ ፡ አልጠማም ፡ ረቻለሁ ፡ ለዘለዓለም
በብርሃኑ ፡ ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጨለማውም ፡ ተሸነፈ
ተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ስላረፈ

እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ
በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፬x)

ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ)
ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ)
እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ)

እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ
በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue