amharic gospel mezmur

ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ አለህ
ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከጫፍ ፡ ሁሉ ፡ እኮ ፡ ግዛትህ
አለቅነት ፡ ስልጣን ፡ ክብር ፡ የአንተ ፡ ብቻ
እናመልክሃለን ፡ ኢየሱስ ፡ የለህ ፡ ብቻ (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x)
የለህም ፡ እኩያ (፬x)

ስግደትና ፡ አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ለሰራዊት ፡ ሁሉ ፡ አለቃ
ለሆንከው ፡ አባታችን ፡ ንጉሣችን (ንጉሣችን)
ፈዋሻችን ፡ ነህ ፡ አዳኛችን ፡ ምርኩዛችን ፡ መታመኛችን
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃገራችን (ሃገራችን)
እንገዛልሃለን ፡ ወድቀን ፡ አዲስ ፡ ቅኔን ፡ እየተቀኘን
ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም ፡ ቅዱስ ፡ አባታችን

ሰማይ ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ መረገጫህ
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ቦታ ፡ አይወስንህ
አሰራርህ ፡ ግሩም ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
አገዛዝህ ፡ ምቹ ፡ ከማንም ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x)
የለህም ፡ እኩያ (፬x)

ስግደትና ፡ አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ለሰራዊት ፡ ሁሉ ፡ አለቃ
ለሆንከው ፡ አባታችን ፡ ንጉሣችን (ንጉሣችን)
ፈዋሻችን ፡ ነህ ፡ አዳኛችን ፡ ምርኩዛችን ፡ መታመኛችን
እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃገራችን (ሃገራችን)
እንገዛልሃለን ፡ ወድቀን ፡ አዲስ ፡ ቅኔን ፡ እየተቀኘን
ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም ፡ ቅዱስ ፡ አባታችን

የጥበብ ፡ ሁሉ ፡ ምንጭ ፡ የዕውቀት ፡ መሰረት
የሰላም ፡ የደስታ ፡ የፍቅር ፡ ተምሳሌት
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለእኛስ ፡ ማረፊያችን
እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ብሩኩ ፡ ተስፋችን (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x)
የለህም ፡ እኩያ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue