Adonay (አዶናይ)

ከሰማይ ፡ ነበር ፡ የተላከ ፡ ከሰው ፡ ተወልዶ ፡ ለሰው ፡ ሞተ
ከሞት ፡ ተነሳ ፡ ከእዛ ፡ አረገ ፡ ከአባቲ ፡ ቀኝ ፡ ተቀመጠ
ለዘመናት ፡ ቀል ፡ የነበረ ፡ ከእቅፉ ፡ ወጥቶ ፡ መጥቶ ፡ ተረፈ
አባትን ፡ ከልጅ ፡ ያስታረቀ ፡ ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ጌታ ፡ የታለ

አሃሃ ፡ አዶናይ (፬x)
የለም ፡ እንዳንት ፡ ምድር ፡ ላይ
የለም ፡ እንዳንተ ፡ በሰማይ (፪x)

ለሁለት ፡ ጌቶች ፡ ለመገዛት ፡ ህጉ ፡ አይፈቅድም ፡ ይከለክላል
አንዱን ፡ ይይዛል ፡ ያን ፡ ይተዋል ፡ ለፈቀደለት ፡ ባርያ ፡ ይሆናል
ሚስጥሩ ፡ ገብቶኝ ፡ መረጥኩኝ ፡ ሌላውን ፡ ትቼ ፡ እርሱን ፡ ሾምኩኝ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ሲሆንልኝ ፡ የቀረው ፡ በሥሙ ፡ ተገዛልኝ

ኢየሱሴ ፡ በእኔ ፡ ላይ (፬x)
አድርጌሃለሁ ፡ የበላይ (፬x)

እስኪ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ የትኛው
በፊቱ ፡ ከብዶ ፡ ሚታየው
ሁሉን ፡ ይችላል ፡ ብቃት ፡ አለው
ስለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ የምናገረው
እኔም ፡ አየሁት ፡ በሕይወቴ
ተዛዝ ፡ አውትቶ ፡ ሲሰራ ፡ አንዴ
ታሪክ ፡ ሲነበብ ፡ ቀን ፡ ሲታይ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አልሻዳይ

አይ ፡ ኤሄሄ ፡ አልሻዳይ (፬x)
የለም ፡ እንዳንት ፡ ምድር ፡ ላይ
የለም ፡ እንዳንተ ፡ በሰማይ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue