ዕልልታ (Elelta) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

ልቤም ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ይኅው ፡ አፈለቀ
ውስጤን ፡ አረስርሶ ፡ በዛ ፡ አጥለቀለቀ
መሬትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ውኃ ፡ እንደሚወጣ
ከልቤ ፡ የደስታ ፡ ጩኅት ፡ ዕልልታ ፡ ካፌ ፡ ወጣ

ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው

ያ ፡ አስቸጋሪው ፡ ዝናብ ፡ ክረምቱ ፡ አለፈ
ድምጼን ፡ ላሰማ ፡ ተነሳው ፡ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሠ
ከአለት ፡ ንቃቃትና ፡ ከገደል ፡ መሰሰጊያው ፡
ማልጄ ፡ ልነሣ ፡ ልውጣ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣው ፡

ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በመለከት ፡ እናመስግነው
በበገና ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው
ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በመለከት ፡ እናመስግነው
በበገና ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው

ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው


በግብጽ ፡ ምድር ፡ ውስጥ ፡ በኩር ፡ ሲመታ ፡ በሞት
አንዱ ፡ ሌላውን ፡ እንዳይረዳ ፡ እርሱም ፡ ጋር ፡ ደረሰበት
ምድሪቱም ፡ ስትናወጥ ፡ በለቅሶ ፡ በዋይታ ፡
ደሙ ፡ ከለላዬ ፡ ሆኖ ፡ አሰማለሁኝ ፡ ዕልልታ

ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው
በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው
ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው
በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው

ልቤም ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ይኅው ፡ አፈለቀ
ውስጤን ፡ አረስርሶ ፡ በዛ ፡ አጥለቀለቀ
መሬትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ውኃ ፡ እንደሚወጣ
ከልቤ ፡ የደስታ ፡ ጩኅት ፡ ዕልልታ ፡ ካፌ ፡ ወጣ

ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው

ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው
በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው
ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው
በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው

ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው
ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue