Bekalu Yemigegn (በቃሉ ፡ የሚገኝ)

ተስፋ ፡ ርቆ ፡ ሲዞር ፡ የሚደግፍ ፡ ጠፍቶ
ዘንበል ፡ የሚል ፡ ማነው ፡ እንደጌታ ፡ ራርቶ
ጊዜ ፡ ወቅቱን ፡ አይተው ፡ ሰዎች ፡ ሲቀየሩ
ጌታ ፡ ግን ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ወረት ፡ የለው ፡ ፍቅሩ (፪x)

መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ የሚተጋ ፡ የሚተጋ
አላየሁኝም ፡ በቃሉ ፡ የሚገኝ ፡ የሚገኝ
አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ብቻውን ፡ ታማኝ (፪x)

ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ
ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x)

ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ምኞቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
አንተን ፡ መታመኔ ፡ እኔ ፡ መች ፡ ከንቱ ፡ ነበረ (፪x)

እሰዪ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
ምርኮዬ ፡ በእርሱ ፡ ተመለሰ
ተሞላ ፡ ልቤ ፡ በደስታ
ልዘርም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)

ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ
ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x)

እንግዲህ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ጨለማዬ ፡ በራ
ከሸለቆ ፡ ወጣሁ ፡ ቆምኩኝ ፡ በተራራ (፪x)

ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ ምኞቴ ፡ ያሰብኩት ፡ ተሳካ
አንተን ፡ መታመኔ ፡ እኔ ፡ ልክ ፡ ነበር ፡ ለካ (፪x)

ልክ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልክ ፡ ነው
እንዳለው ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያደረገው
ሁኔታ ፡ ቃሉን ፡ አለወጠው
በእውነትም ፡ ጌታዬ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፪x)

መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ የሚተጋ ፡ የሚተጋ
አላየሁኝም ፡ በቃሉ ፡ የሚገኝ ፡ የሚገኝ
አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ብቻውን ፡ ታማኝ

ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ
ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x)

በሀሩሩ ፡ ጥላ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ
ምስኪን ፡ የምታግዝ ፡ ፀሎት ፡ የምትሰማ
በሀሩሩ ፡ ጥላ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ
እኔን ፡ የምታግዝ ፡ ፀሎት ፡ የምትሰማ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue