እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ (Endante Yale Amlak)

ራስህን ፡ መስዋት ፡ አርገህ ፡ ስለእኛ ፡ ታርደሃል
ለአምላክህ ፡ አዲስ ፡ ሕዝብን ፡ በደምህ ፡ ዋጅተሃል
መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ለአባትህ ፡ አዘጋጀህ
አምልኮ ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ፡
፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ
፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ
፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ አዳኝ ፡ አልተገኘምና
፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና
፡ ይገባሃልና

ከንፈሮችህ ፡ ጠቢብ ፡ በዕውቀት ፡ የላቁ ፡
ጻድቅ ፡ ሆይ ፡ በዕውቀትህ ፡ ብዙዎች ፡ ጸደቁ
ለእግዚአብሔር ፡ ማደሪያ ፡ ቤትን ፡ ሰራህለት ፡
አብም ፡ በአንተ ፡ ስራ ፡ ደስ ፡ ተሰኘበት
፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ
፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ
፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ ጥቢብ ፡ አልተገኘምና
፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና
፡ ይገባሃልና

ነግስታት ፡ ኃያልን ፡ ጠቢባንም ፡ ጭምር
ጌታ ፡ ዝቅ ፡ በለው ፡ ይስጡ ፡ ለአንተ ፡ ክብር
ጐልማሶች ፡ ቆንጆዎች ፡ ሽማግሌዎች ፡ ይምጡ ፡
ለታላቅነትህ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ ይስጡ
፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ
፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ
፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ አልተገኘምና
፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና
፡ ይገባሃልና

ከመላእክት ፡ በላይ ፡ ከነቢያት ፡ በላይ
ከሊቀ ፡ ካህናት ፡ ከአባቶችም ፡ በላይ
ተሹመህ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀምጠሃል
አምልኮ ፡ ውዳሴ ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል
፡ ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ይብዛልህ
፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥህ
፡ እንዳተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ አልተገኘምና
፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልህ ፡ አምልኮ ፡ ምሥጋና
፡ ይገባሃልና

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue